የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 1439ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ

Monday, 20 August 2018 13:53

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 1439ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዩች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡
አዲስ አበባ የአረፋበዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች አንዷ ነች፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የእምነቱ ተከታዩች በጋራ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሶላት ያደርጋሉ፡፡ በሶላት ወቅትም ይሁን ከዚያም በኋላ በዓሉ በሰላም እንዲያከበር ፖሊስ ኮሚሽኑ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡
በበዓሉ እለት በአዲስ አበባ ስታዲዩም እና በዙሪያው ፍተሻ መኖሩን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፍተሻ እንዲተባበር ፤ የእምነቱ ተከታዩች ለሶላት ሲመጡ የስለት መሳሪያዎችን እና ሌሎችአዋኪ ነገሮችን ይዞ ባለመምጣት የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ከፍተኛ አስተዋእፆ ማበርከቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ የዘንድሮ የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቀርቧል፡፡arefa


በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚደረገውን የሶላት ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-
• ከቦሌ ኦሎምፒያ  ፍላሚንጎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኡራኤል ባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ  ብሄራዊ ቤተ-መንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን
• ካሳንቺስብሄራዊ ቤተ-መንግስትፍልውሃ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ኦርማ ጋራዥ ፍልውሃ ሐራምቤ ሆቴል
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ኢሚግሬሽን ሐራምቤ ሆቴል ስታዲዬም
• ከጎማ ቁጠባ ብሄራዊ ቲያትር ስታዲዬም
• ከሰንጋ ተራ በድሉ ህንፃ  ስታዲዬም
• ከሰንጋ ተራ በለገሃር ስታዲዬም
• ከሜክሲካ አደባባይ በለገሃር ስታዲዬም
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድበለገሃር ስታዲዬም
• በሐራምቤ ሆቴል  ጋንዲ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጎተራ  በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ
ከቦሌ ወደ ኣራት ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
በኡራኤል በካሳንቺስ አራት ኪሎ
ከመገናኛ ወደ ጦር ኃይሎች መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
በኡራኤል  ካሳንቺስ ታላቁ ቤተ-መንግስት  እሪበከንቱ ቴዎድሮስ አደባባይ ኤክስትሪም ሆቴል  ተክለ ሀይማኖት  ጣር ሀይሎች
ከሳሪስ አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ እና ፒያሳ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ጎተራ  ወሎ ሰፈር  አትላስ ሆቴል  ኡራኤል  ካሳንቺስ  አራት ኪሎ ያሉ መንገዶችን በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡
ከዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ማታ ጀምሮ የሶላቱ ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ድረስ በስታዲዬም ዙሪያ እና አካባቢው በግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ ለጸጥታ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ከፈለገ በስልክ ቁጥሮች-
• 011-5-52-63-03
• 011-5-52-40-77
• 0115-52-63-02
• 011-1-11-01-11
ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዩች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡

Last modified on Monday, 20 August 2018 14:05
Rate this item
(1 Vote)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus