wanaw User

wanaw User

policenews

በአ/አበባ ከተማ በተለያዩ ክ/ከተሞች ጊዜ ተወስዶ በተደረገ ሰፊ ጥናት ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች በ88 የተለያዩ የወንጀል ፈፃሚዎች ቡድን የተደራጁ 216 ግለሰቦች መሆናቸውን የገለፁት በኮሚሽኑ የኢኮኖሚና የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዲቪዚዮን ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር አበራ ቡሊና ናቸው፡፡

ሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ/ም በቢሯቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራሩት ጊዜ በወሰደው ጥናት ከቅሚያ ወንጀል ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያለው የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችና የኢትዮጵያ ብር እንዲሁም የተለያየ ደረጃ ያላቸው አደንዛዥ እፆች ከግለሰቦቹ ጋር ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ጨምረው ገልፀዋል፡፡


ለስራው ውጤታማነት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠትና ጥቆማ በማድረግ ያደረገው ትብብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረው የገለፁት ኃላፊው ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው ብለዋል፡፡

መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትሉት ተፅእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ፖሊስ ቀጣይነት ያለው ሰፊ ጥናቶችን በማድረግ ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልፀው የህብረተሰቡ ትብብር በቀጣይነትም ለፖሊስ ስራ ወሳኝ በመሆኑ ትብብሩ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡  

በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ሃዋስ ወረዳ ላይ በሚገኘው የደብል ተራራ ላይ የኮሚሸኑ አመራርና አባላት የችግኝ ተከላ ያካሄዱት ሐምሌ 23 ቀን 2009 ዓ.ም ነው፡፡ በዕለቱ ‹‹ ለአረንጓዴ ልማታችን ስኬታማነት ሁሌም በትጋት እንሰራለን ›› በሚል መሪ ቃል በተደረገው የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአ/አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ተስፋዬ ደንደና እንደገለፁት ከ2005 ዓ.ም በፊት የተራቆተውን የደበል ተራራ መልሶ ለማልማት የኮሚሽኑ አመራርና አባላት ለተከታታይ 4 አመታት ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ስፍራው ከመልማቱ በጠጨማሪ ለአካባቢ ወጣቶች ኮሚሽኑ የለገሳቸው የንብ ቀፎ በምን ደረጃ እንዳ በጤና ጥበቃ ሚንስተር ዴታና መ/ኮሚሽነር ተስፋዩ ደንደና ተጎብኝቷል፡፡ በችግኝ ተከላው ፕሮግራም ላይ የተገኙ የፖሊስ አመራርና አባላት ከ45 ሺ ችግኞች በላይ መትከላቸውን በዕለቱ ተገልጿል፡፡ 

newsplantation

 

የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተማውን ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቁ በተጨማሪ በአካባቢያቸው እያደረገ ያለው የአረንጓዴ ልማት ስራውን የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል ሲሉ የሃዋስ ወረዳ ነዋሪዎች ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡ 

 

 

ሃይሉ ቡናሮ ወንጀሉን የፈፀመው ግንቦት 27 ቀን 2009 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የአ/አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት መነሻ ፌርማታ አካባቢ ነው፡፡

ንብረት

ተከሳሹ በተጠቀሰው ቀን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በመግባት ግምታቸው 6 ሺ 3 መቶ ብር በላይ የሚያወጡ 4 የእሳት ማጥፊያዎችን ከሰረቀ በኋላ እስክ ነጋ ባቡር በመጠበቅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶት ከነንብረቱ መያዙን የፌ/ጠ/ዐ/ህግ አቶ አብርሃም አያሌው ገልፀዋል፡፡

በተከሳሹ ላይ የተደራጀውን የምርመራ መዝገብ የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት በነሀሴ 27 ቀን 2009 ዓ/ም ውለው ሃይሉ ቡናሮን ጥፋተኛ በማለት በ1 አመት ከ8 ወር እስራት እንድቀጣ የወሰነበት መሆኑን የምርመራው መዝገብ ያስረዳል፡፡

መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለወንጀል መፈፀም ምቹ የሆኑ ንብረቶቻቸውን በተገቢ ሁኔታ እንድጠበቁ በማድረግ ወንጀልን አስቀድመው ሊከላከሉ እንደሚገባ ሃላፊው ገልፀዋል፡፡

ወንጀሉ የተፈፀመው የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ልዩ ቦታው ላፍቶ ባንኮች ማህበር እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ሟች አቶ ተወልደ ገ/አምላክ በመኖሪያ ቤታቸው መኝታ ክፍላቸው ውስጥ ተኝተው እያለ እንዲሁም የቤት ሰራተኛቸው ሟች ትህትና ውብሸት የተባለችው ደግሞ በሌላኛዋ መኝታ ክፍል ውስጥ ተኝተዋል፡፡

የሟች ዘመድ የሆነው ተከሳሽ በቅርቡ በሟች ቤት በእንግድነት መጥቶ ከአቶ ተወልደ ጋር እየኖረ ነበር፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ቤቱ ውስጥ ያሉትን ንብረቶች ካጠና በኋላ የመኖሪያ ቤቱን የበር ቁልፍ በእጁ በማድረግ ቤቱን ለመዝረፍ ከሌሎች ግብረ አበሮች ጋር በመስማማት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ሟች አቶ ተወልደ ከመኝታቸው የቅርብ ዘመዳቸው ተጠርጣሪ የሻወር ቤቱ ውሃ እየፈሰሰ ነው በሚል ምክንያት ከጠራቸው በኋላ በገጀራ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ በሌላኛው መኝታ ክፍል የተኛችውን ሟች ትህትና ውብሸትን ከተኛችበት ቀስቅሰው የተፈፀመውን ድርጊት አይታለች ለፖሊስ ትናገራለች በሚል ሰበብ በተመሳሳይ ሁኔታ እሷንም ከገደሏት በኋላ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ያገኙትን ጥሬ ገንዘብ ላፕቶፕ ሁለት ታፕለት ሞባይሎችና ካሜራ እንዲሁም የሟች አልባሳትና ጫማ በመውሰድ የመኖሪያ ቤቱን በር ዘግተው ይሰወራሉ፡፡

ሟች አቶ ተወልደን ለ2 ቀናት በአካባቢው ያጡ ጎሮቤቶች ተጠራጥረው ለዘመዶቻቸው በመደወል እንደሌሉ በመግለፃቸው ቁልፍ በማስመጣትና ለፖሊስ በመደወል የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ/ም የመኖሪያ ቤቱ በር ሲከፈት ሞተው በመገኘታቸው ምርመራው እንደተጀመረ የነገሩን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ምርመራ ክፍል መርማሪ ዋና ሳጅን መንግስቱ ታደሰ ናቸው፡፡

ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ዋና ሳጅን እንደገለፁት ወንጀሉን ማንይፈፅማል የሚለውን የክትትል ቡድኑና የምርመራ ክፍሉ በመ ቀናጀት ባደረጉት ጥረት 2ቱን ወንጀል ፈፃሚዎች በመያዝና በመመርመር ወንጀሉን እንደፈፀሙ በማመን ኢግዚቢቶች እንደተያዘባቸው ተናግረዋል፡፡

እንደ መርማሪው ገለፃ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላካቸውን ገልፀው ያልተ ያዙትን ተጠርጣሪዎች እና ንብረት ለማስመለስ ጥረት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የሟች አቶ ተወልደ ቤተሰቦችን አግኝተን ባነጋገርንበት ወቅት ወንጀል ፈፃሚዎቹ ይያዛሉ ብለው እንዳላሰቡ ገልፀው በአጭር ጊዜ ውስጥ ማንነታቸው ታውቆ በመያዛቸው እንደተሰቱ ተናግረዋል፡፡  

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus