አንዲት እናት አርሶ አደር ባበረከቱት 250 ካሬ ሜትር.... Featured

Friday, 12 March 2021 08:08

አንዲት እናት አርሶ አደር ባበረከቱት 250 ካሬ ሜትር መሬት ላይ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባው የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ማዕከል ተመርቆ ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአርሶ አደሯ ተግባር ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
*****************
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ መድሃኔዓለም እየተባለ በሚጠራ አካባቢ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ6 መቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ማዕከል ተገብቶ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ተመርቋል፡፡
በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አድማሱ ኢፋ ባደረጉት ንግግር የአካባቢው ህብረተሰብ ለማዕከሉ ግንባታ ላደረገው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡በተለይ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን መሬት ከግል ይዞታቸው ላይ ቆርሰው 250 ካሬ ሜትር የሰጡት ወ/ሮ ቀነኣ በዳዳ የፈፀሙት ተግባር ለሌሎች በአርዓያነቱ የሚገለፅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡አርሶ አደሯ ለማዕከሉ ግንባታ እንዲውል መሬቱን መፍቀዳቸው ህብተሰቡ ለአካባቢው ሠላም እውን መሆን ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ያሉት ኃላፊው ፖሊሶችም ኃላፊነታችን በብቃት እንድንወጣ የሚበረታታን ነው ብለዋል፡፡
ለመሆኑ የግል ይዞታዎን ለመስጠት ያነሳሳዎ ጉዳይ ምንድ ነው? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ከሠላም የሚበልጥ ነገር የለም ያሉት አርሶ አደሯ ሠላም ካለ የቀረኝ ይዞታ ቢቀ ነው ካሉ በኋላ በቀጣይም የአካባቢዬን ሠላም ለማስጠበቅ ከፖሊስ እና ከጸጥታ ኮሚቴው ጋር ጠንክሬ እሰራለሁ ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ቀነኣ በዳዳ ባበረከቱት 250 ካሬ ሜትር ላይ ከ6 መቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የወጣበት ደረጃውን የጠበቀ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ማዕከል ተገንብቷል፡፡
በመጨረሻም ኮማንደር አድማሱ ኢፋ አርሶ አደሯም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦችና ተቋማት ለማዕከሉ ግንባታ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በዕለቱ አርሶ አደሯ የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ለግንባታው ስኬታማነት ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅና ተሰጥቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ምክትል ሳጅን አዳነ ደስታ

Rate this item
(1 Vote)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus