
የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ምኒልክ አደባባይ በተመሳሳይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የተከበረው እና የድል በዓሉን አስመልክቶ መነሻውን ምኒልክ አደባባይ መዳረሻውን አድዋ ድልድይ የተደረገው የእግር ጉዞ በደማቅ ሁኔታ በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
125ኛው የአድዋ የድል በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
በያዝነው የበጀት ዓመት የተከበሩ ሃይማኖታዊ እና ብሔራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
