አዲስአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለ22ኛ እና ለ23ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ምልምል ፖሊስችን አስመረቀ፡፡ Featured

Friday, 12 March 2021 11:49
 
 
 
ምናልባት የ1 ሰው፤ ቆመዋል እና ከቤት ውጪ ምስል
 
ኮልፌ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፖሊስ አካዳሚ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 1516 ምልምል ፖሊሶች የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የከተማው የካቢኔ አባለት ፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሌች እንግዶች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡
በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት ለሰላም እና ለህግ የበላይነት እውን መሆን የፀጥታ አካላት ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ገልፀው የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ፤ ሰዎች ከወንጀልና ከትራፊክ አደጋ ስጋት ነፃ ሆነው በሰላም የእለት ከእለት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ተልዕኮ የተጣለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለውጡን ተከትሎ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በፀጥታ ስራ ይሁን በልማት ስራ ላይ ህዝብን ማሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ ምክትል ከንቲባዋ አስገንዘበው ኮሚሽኑ ለተልዕኮ ስኬታማነት የነዋሪውን አቅም ለመጠቀም እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አበረታች በመሆኑ አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል ብለዋል፡፡
በቅርቡ 6ኛ ሃገር አቀፍ ምርጫ እንደሚካሄድ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውሰው ፖሊስ ለምርጫው ስኬታማነት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ መልዕከታቸውን አስተላልፈው የከተማው አስተዳደር የኮሚሽኑን አቅም ለማጎልበት እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
ፖሊሶች መልካም ስነ-ምግባርን ተላብስው ተገቢውን አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚገባ የተናገሩት ምክትል ከንቲባዋ የዛሬ ተመራቂ የፖሊስ አባላትም ህግና ህግን መሰረት በማድረግ ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ለውጡን ተከትሎ የተቋሙን አቅም ለማጎልበት የሪፎርም ስራ እንደተሰራ ተናግረው የፖሊስን አገልግሎት ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ የፖሊስ ጣቢያዎችን ቁጥር 60 ማድረግ እንደተቻለ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የጣቢያዎቹን ቁጥር 120 ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን ለመወጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን በተለይ በህግ ማስከበር ተልዕኮ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የአስተዳደር እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተሰራ ተግባር ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡
በፀጥታ ስራ ላይ የህዝብን ተሳትፎ ማሳደግ በመቻሉ ፣ ከአስተዳደር ፣ ከሌሎች የፀጥታ እና የፍትህ አካላት ጋር ያለው ትስስር እንዲጠናከር በመደረጉ እንዲሁም የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎችን በተገቢው መንገድ መምራት በመቻሉ የተሸከርካሪ ስርቆት እና ከባድ ወንጀል መቀነሱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
6ኛ ሃገሪዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኮሚሽኑ ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ፤ የፖሊስ አመራሮችና አባላት በምርጫ ወቅት ሊከተሉት የሚገባውን ስነ-ምግባር በተመለከተ መመሪያ ተዘጋጅቶ ስልጠና እንደሚሰጥ ከኮሚሽነር ጌቱ ንግግር መረዳት ተችሏል፡፡
ተቋሙን ለማዘመን ሆነ አቅሙን ለማጎልበት በሚሰሩ ስራዎች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ነው ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ በጀት በመመደብ ፣ ለግንበታ የሚሆኑ ቦታዎችን በመፍቀድ በጥቅሉ አስፈላጊ ድጋፍ እያደረገ ላለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናው እንዲሳካ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ምልምል ፖሊሶችም ከስልጠናው ያገኙትን እና ከነባር አባላት የሚያገኙትን እውቀት በአግባብ ተጠቅመው ስራቸውን በተገቢው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ከለውጡ በፊት መሰል ስልጠናዎች ከአዲስ አበባ ውጭ ይሰጡ እንደነበረ ለውጡን ተከትሎ በተሰሩ ስራዎች አካዳሚውን ለስልጣና ምቹ ማድረግ በመቻሉ አብዛኞቹ ስልጠናዎችን በአካዳሚው ውስጥ መስጠት እንደተቻለ እና ከመደበኛ ፖሊሳዊ ስልጠናዎች በተጨማሪ ልዩ ልዩ የሙያ ስልጠና በአካዳሚው እየተሰጠ እንደሆነ የአካዳሚው ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር መኮንን አሻግሬ ስልጠናውን እና ፖሊስ አካዳሚው ያከናወናቸውን ስራዎች በተመለከተ ካቀረቡት ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡
በዛሬው የምርቃት ፕሮግራም መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠናን ያጠናቀቁ ወንድ 1110 ሴቶች 406 በድምሩ 1516 ምልምል ፖሊሶች ስልጠናቸው አጠናቀው ተመርቀዋል፡፡
ፖሊስነት ከራስ ይልቅ የህዝብን ጥቅምን ማስቀደም የሚጠይቅ ሙያ መሆኑን በስልጠና ወቅት መገንዘባቸውን እና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸው ያነጋገርናቸው ተመራቂ የፖሊስ አባላት ተናግረዋል፡፡ በፕሮግሙ ላይ የሰልፍና ልዩ ልዩ ትሪኢቶች በተመራቂ የፖሊስ አባላት ቀርቧል፡፡ምናልባት የ2 ሰዎች እና የቆሙ ሰዎች ምስልምናልባት የአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች፤ የቆሙ ሰዎች፤ people walking እና ከቤት ውጪ ምስልምናልባት የአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች፤ የቆሙ ሰዎች እና ከቤት ውጪ ምስልምናልባት የቆመዋል እና ከቤት ውጪ ምስል
Rate this item
(1 Vote)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus