የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው አመራሮችና አባላት በሦስት ዙር የሠጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀቀ፡

Monday, 22 April 2019 08:10

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው አመራሮችና አባላት በሦስት ዙር የሠጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀቀ፡፡ ወቅቱ የሚጠይቀውን ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው ገልፀዋል፡፡3
በኮሚሽኑ ከመጋቢት 9 እስከ ሚያዚያ 9 ቀን 2011 ዓ/ም በሦስት ዙር ለመላው አመራሮችና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ሚያዚያ 10 ቀን 2011 ዓ/ም በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የፀጥታ አካላትን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 2
ኮሚሽነር ጀነራሉ አያይዘው ሀገራችን በለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝድ እና ለውጡ ህዝባዊና ህገ-መንግስታዊ መሆኑን በመጥቀስ በህዝብ ፍላጎት የመጣው ለውጥ የታለመለትን ግብ እንዲመታ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡3
ለውጡ በፖሊስ ተቋማት ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የጠቁሙት ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከምንም በላይ ለሰው ሀብት ልማት እና ለኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የፖሊስ አመራሮችና አባላት የለውጡን ባህሪ ተገንዝበው በተለይ ሰብዊ መብቶችን አክብረው በማስከበር ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ህዝብና መንግስት ቅን አገልጋይ እንደሚፈልጉ ተናግረው ኮሚሽኑ የለውጡ አካል በመሆን ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የፖሊስ ተቋም በመገንባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገችና እየዘመነች ለምትገኘው ከተማችን የሚመጥን የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ 54
ስልጠናው የአመራሮችን እና የአባላትን የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት የራሱ ጠቀሜታ ማበርከቱን ኮሚሽነር ጌቱ በንግግራቸው ጠቁመው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በቅርበት ከሚሰሩ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎ ሺፕ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ ልዩ ልዩ መልክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን ተቋማቸው ለፀጥታ አካላት የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡በአስራ ሦስት የተለያዩ ስፍራዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተደግፎ በተሰጠው ስልጠና ላይ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ስልጠናውን ተከታትለውታል፡፡

Rate this item
(3 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus