የካቲት 17- 20 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን ለ2013 ዓ.ም ያዘጋጀውን የ2ኛ ዙር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክለቦች ቦክስ ሻምፒዮና የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የተሳተፈው የአዲስ አበባ ፖሊስ ቦክስ ቡድን በወንዶች 49ኪሎ ብር በ57 ኪሎ ወርቅ፤በ60 ኪሎ ወርቅ ፤በ69 ኪሎ ወርቅ ፣ በ75 ኪሎ ያለነጥብ ወርቅ፤በ81 ኪሎ ወርቅ በድምሩ በ14 ነጥብ ከ 7 ክለቦች መካከል 1ኛ በመሆን የዋንጫና የሜዳልያ ተሸለሚ ሲሆን በሴቶች በ51 ኪሎ ብር፣ በ57 ኪሎ ወረቅ ፣በ60 ኪሎ ብር በድምሩ ከ 4 ክለቦች መካከልበ 7 ነጥብ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን በስኬት አጠናቋል።
መረጃውን ያደረሰን፡- ኢንስፔክተር ቴዎድሮስ አበበ ( ጎንደር)