ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሃገር ቤት የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች አዲስ አበባ ፍፁም ሰላም የሰፈነባት ከተማ መሆኗን ማረጋገጣቸውን ተናገሩ፡፡በመላው ሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ Featured

Thursday, 06 January 2022 11:16

ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሃገር ቤት የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች አዲስ አበባ ፍፁም ሰላም የሰፈነባት ከተማ መሆኗን ማረጋገጣቸውን ተናገሩ፡፡በመላው ሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
*******
ኢትዮጵያ ተጣርታ አልቀርም በማለት ኑሯቸውን በተለያዩ ሃገራት ያደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሃገር ቤት በመግባት ላይ ናቸው፡፡
የዲያስፖራው ማህበረሰብ በቃ ወይም # NO MORE በሚል ጠንካራና ተከታታይ ሰልፍ በማድረግ የኢትዮጵያ ልሳን በመሆን የሀገራቸውን ድምፅ ሲያሰሙ መቆየታቸው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ሊቀመንበር አቶ እንድሪስ መሃመድ በተለይ ለአዲስ ፖሊስ ገልፀዋል፡፡ ማህበራቸው ልዩ ልዩ ሃገራዊ ጉዳዮችን በማስተባበር በውጪ የሚገኙ ዜጎች ለሃገራቸው እድገት እና ልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በአውሮፓ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አስተባባሪ አቶ ሰለሞን አሻግሬ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ሃገራችንን ያጋጠማትን ችግር ለመቅረፍ መላው ህዝብ እየተረባረበ እንደሆነና የዲያስፖራው ማህበረሰብም የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን በማስታወስ አሁን የተጀመረው የሃገርን ጥቅም የማስጠበቅ እንቅስቃሴን አጠናክረን በመቀጠል የሃገራችንን ችግር በዘላቂነት ልንፈታ ይገባል ብለዋል፡፡
ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ሚኒሶታ የሆነው ወ/ሮ ዘኒ ተሾመ ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት እንደመጡና እየተደረገ ባለው አቀባበል በጣም መደሰታቸውን አስረድተው ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ የገና በዓልን ለማክበር ወደ ላሊበላ ለመሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የመምጣታቸው ዋነኛ ምክንያት ስለ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት የሚነገረውን የተዛባ መረጃ ሃሰት መሆኑን ለመላው ዓለም ለማሳወቅና ለሃገራቸው እና ለወገናቸው ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት እንደሆነ ከአዲስ ፖሊስ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ሃሳባቸውን አጋርተውን ይህን በማድረጋቸውም ሀገራዊ ኩራት እንደተሰማቸው እንግዶቹ ገልፀዋል፡፡
የዲያስፖራ አባላቱ በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበው ከተማችን አዲስ አበባ ፍፁም ሰላም የሰፈነባት እንደሆነች በተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋውረው ማረጋገጣቸው አስታውቀው በመላው ሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡1111

Rate this item
(2 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus