ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ሊዘዋወር የነበረ ጥይት በሕብረተሰቡ ጥቆማ ከእነ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ጥይቱ የተያዘው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ክልል ልዩ ቦታዉ አየር ጤና አውቶቢስ ተራ መናሃሪያ ግቢ ዉስጥ ነዉ፡፡

አንድ ግለሰብ ብዛቱ 394 ጥይት በመዳበሪያ ጠቅልሎ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ከተሞች ይዞ ለመሄድ ሲሞክር አየር ጤና መናኸሪያ ውሰጥ በአሽከርካሪው እና በረዳቱ በተደረገ ፍተሻ ተጠርጣሪው ከእነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡bullet

በአሁን ወቅት በሃገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች እየተስተዋለ የመጣዉን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ከመከላከል በተጨማሪ ሊያስከትል የሚችለዉን ጉዳት በመረዳት ህ/ሰቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን እያደረገ ያለዉን ጥረት  አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ 

በርበሬነው በማለት የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጠራባቸው ነው፡፡ መሰል ወንጀሎችን በመከላከል ዙሪያ የመናኸሪያ ሰራተኞ እያደረጉት ያለው አስተዋዕፆ ሊበረታታ ይገባል ተብሏል፡፡

kash vs berbereበወንጀሉን የተጠረጡት ግለሰቦች ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ለሊት ከንጋቱ 11፡30 ሠዓት ላይ የተለያዩ  የጦር መሳሪያዎችን በርበሬ ነው በማለት በሁለት ማዳበሪያዎች ውስጥ አድረገው በህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ ለማስጫን ሲሞክሩ  በጫኝና አውራጅ ስራ ላይ የተሰማሩ ተጠራጥረው ባደረጉት ፍተሻ መሳሪያዎቹን ከነተጠርጣዎቹ ይዘው ለፖሊስ ማስረከባቸውን ከአዲስ ፖሊስ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተው እያንዳንዱ ሰው ለሀገሩ ሰላም ሲል አስፈላጊውን ትብብር ሊያርግ ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡klash

የጉዳዩ መርማሪ ም/ ሳጅን ዳኛቸው ለገሰ እንደተናገሩት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ክልል በሚገኘው ትልቁ መናኸሪያ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በተደጋጋሚ ጊዜ ተመሳሳይ ወንጀሎች እንደሚፈፀም አስታውሰው በአውቶቢስ ተራው ውስጥ  በጫኚና አውራጅ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች  በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተሰማሩ ግለሰቦችን በተደጋጋሚ ጊዜ እጅ ከፍንጅ ይዘው ለፖሊስ ማስረከባቸው የሚበረተታ ስለሆነ ተግባሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡   

አንዳንድ ግለሰቦች ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ፖሊስ ገለፀ፡፡ ሰልፉ በከተማው አስተዳደር ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ ስፍራዎች ከፀጥታ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እንዲሁም የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ ታህሳስ 6 እና እሁድ ታህሳስ 7/2011 ዓ/ም አንዳንድ ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩም ይሁን በፖሊስ እውቅና የሌለው መሆኑን የኮሚሽኑ ኢንዶክተሪኔሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ከላከው ዜና መረዳት ተችሏል፡፡logo

ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ-መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሞ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑን ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑመልእክቱን አስተላፏል፡፡

በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

በዓለም አቀፍ 31 በሀገር አቀፍ 30 ጊዜ የተከበረውን የኤች.አይ. ኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ለፖሊስ አመራሮችና አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡hivday1

የስልጠናው ተከፋዩች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ልገሳ እና የኤች.አይ. ምርመራ አደረጉ፡፡ "ለኤች.አይ. ኤድስ ይበልጥ ተጋላጭ ነን፣ እንመርመር እራሳችን እንወቅ" በሚል መሪ ቃል ህዳር 28 ቀን 2011 . በኮሚሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማሥጨበጫ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ጤንነቱ የተጠበቀ የህዝብ አገልጋይ የፖሊስ አባላት እንዲኖር ኮሚሽኑ አበክሮ እንደሚሰራ ገልፀው ሁሉም አመራርና አባላት ከተላላፊ በሽታዎች እራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው መልእክት አሳስበዋል፡፡hivdat2

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች.አይ. ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር /ቤት ኃላፊ ሲስተር ብርዛፍ ገብሩ በበኩላቸው ኤች.አይ./ ኤድስ በሀገራችን በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችን እያስከተለ መሆኑን አስታውሰው በተለይ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል በቫይረሱ እየተጠቃ ስለሆነ ስርጭቱን ለመግታትና ለመቆጣጠር ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የበሽታው ሰለባ መክረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ኮሚሽነር ዮሐንስ ጭልጆ አብዛኛው የኮሚሽኑ አባላት በወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ በመሆናቸው ራሳቸውንና ሌሎችን ከኤች. አይ. ኤድስ በመከላከል ሀላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለው ኮሚሽኑ ከአዲስ አበባ የኤች አይ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር /ቤት ጋር ያለውን ቁርኝት አጠናክሮ በመቀጠል መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

ማዕከልን ጨምሮ ከአስሩ /ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለተውጣጡ አመራርና አባላት በቅድመ መከላከል ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች.አይ. ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር /ቤት ባለሙያ በሆኑት ሲስተር ሽብሬ መንገሻ አማካኝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሌላ መልኩ የፖሊስ አመራር እና አባላቱ በደም እጦት ምክንያት ወገኖቻችን ህይወቻችን እንዳያጡ ለኢትዮጵያ ደም ባንክ አገልግሎት ደም የለገሱ ሲሆን በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች.አይ./ኤድስ ምርመራ አድርገዋል፡፡hivday5hivday4

የጀርመን ፖሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡ የጀርመን ፖሊስ ለኮሚሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጾል፡፡

ህዳር 25ቀን 2011 ዓ.ም የጀርመን ፖሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩርገን ሹበርት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡jer 1

በውይይቱ ላይ ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በእድገቷ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከምትገኘው የጀርመን ሀገር ፖሊስ የሀገራችን የፖሊስ ተቋማት በርካታ መልካም ተሞክሮዎችን መቅሰም እንደለባቸው ተናግረው የሁለቱ ሀገራት ፖሊሶች የቀደመ ግንኙነት እንዳላቸው እና ጀርመን የኢትዮጵያን ፖሊስ ለማጠናከር ልዩ ልዩ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን በማስታዎስ አሁንም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡  jer 2

የጀርመን ፌደራል ፖሊስ ምክትል ፕሬዚዳንት ዩርገን ሹበርት በበኩላቸው ኢትዮጵያ በለውጥ ጉዳና ላይ መሆኗን መረጃ እንደላቸው ገልፀው የሀገሪቷን የፖሊስ አቅም ለማጎልበት እና ተባብረው መስራት በሚያስችልበት ጉዳይ ዙሪያ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያን ፖሊስ አቅምን ለማጎልበት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡jer 3

ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሊገባ የነበረው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሱሉልታ ኬላ ላይ በአዲስ አባበ ፖሊስ በሻለቃ አራት የወንጀል መከላከል ተወርዋሪ ሃይል አባላት እና በብሄራዊ ደህንነት ሰራተኞች 9120(ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ሃያ ) የክላሽ ኮቭ ጥይት እና 39600 ብር (ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ)ብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡bullet

ህገ ወጥ የጦር  መሳሪያው እና ገንዘቡ ሊያዝ የቻለው በቅድመ ህብረተሰብ ጥቆማ አማካኝነት ነው፡፡ የከተማችን አዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈንና የህግ የበላይነትንለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከህብረተሰቡና ከሚመለከተቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እያደረገ ያለው የወንጀል መከላከል ተግባር የሚበረታታ ነው፡፡ በተለይ ሰፊው የህብረተስብ ክፍል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን አስቀድሞ በመጠቆም በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ ረገድ  ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡bulle mobullet 1

በአ/አበባ  ከተማ  የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ፍሰቱን ለማሳለጥ የሚያግዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  አስታወቀ፡፡

በከተማችን አ/አበባ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ዘወትር የሚታየው የትራፊክ መጨናነቅ አሽከርካሪውና የመንገድ ተጠቃሚው ባቀደው ሰዓት ጉዳዩን እንዳይፈፅም ምክንያት እየሆነ መምጣቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይም ዋና ዋና በሚባሉ የከተማው መንገዶች ላይ በሥራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓታት ችግሩ ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡2

            የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከከተማው መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው በተመረጡ ቦታዎች ላይ ፍሰቱን የማሳለጥ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ህዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም የኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ፍሰቱ ከሚበዛባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ በሆነው በሀያት መገናኛ መስመር ላይ ከህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ፍሰቱን ሠላማዊ የማድረግ ተግባር ተጀምሯል፡፡1

አንዳንድ አሽከርካሪዎች በሰጡት አስተያየት የትራፊክ መጨናነቁን ለማሳለጥ በጊዚያዊነት የተሰራው ስራ ሊበረታታ የሚገባው ቢሆንም በዘላቂነት መፍትሄ የሚያሻው ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

እንደ ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ገለፃ የከተማው አስተዳደር ለረጅም ዓመታት ያለምንም ልማት ታጥረው የተቀመጡ  ቦታዎችን ወደ ልማት እንዲገቡ ቅድመ ዝግጅት  እያደረገ መሆኑን ገልፀው በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በማዘጋጀት ዘለቄታነት ያለው ሠላማዊ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ  አብራርተው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፍሰቱን ቀልጣፋ ለማድረግ በሚሰራው ስራ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡  34

ዕውቅናና ማበረታቻ ተሰጠ!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በስራ እንቅስቃሴዎቻቸው ጎልተው በመውጣት ከተጠርጣሪዎች የገንዘብ መደለያ አንቀበልም ሲሉ ለህግ በማቅረብ ለሰሩት አኩሪ ተግባር ለአመራርና ለአባላቱ የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡ መስከረም 12 እና መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም በተዘጋጀው የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ኮሚሽነር ደግፌ በዲ የከተማዋን ነዋሪዎች የፍትህ ጥያቄ በአግባቡ ሊመልስ የሚችል የፖሊስ ኃይል ለመፍጠር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው ለተሸላሚዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ም/ኮሚሽር ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው መንግስት የጥቁር ገበያን ለመግታት በጀመረው ዘመቻ የኮሚሽኑ አባላት ከሁለት ሚሊየን እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር ድረስ ከተጠርጣሪዎች የቀረበላቸው መደለያ ሳያጓጓቸው ተጠርጣሪዎችን ለህግ በማቅረባቸው የፖሊስ ተቋሙን ያኩሩ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም መሰል ማበረታቻዎች እንደሚቀጥሉ ገልፀው አዳዲስ የፖሊስ አባላትም ከዚህ አርአያነት ካለው ተግባር ብዙ ትምህርት ሊማሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የፖሊስ ስራ በትልቅ መስዋዕትነት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን የጠቀሱት የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ም/ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ ይህ ማበረታቻ ሙያዊ ስነ ምግባራቸውን ጠብቀው ለሚሰሩ አባላትና አመራሮች ትልቅ ብርታት ነው ብለዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የ20ኛ ዙር የፖሊስ አባላት አቀባበል የተደረገ ሲሆን የፖሊስ አመራሩና አባላቱ ላከነወኑት ተግባር አድናቆታቸውን ገልፀው አርአያነታቸውን እንደሚከተሉም ተናግረዋል፡፡
com.shilmatcom2 shilmatshilmat 2

*********************************
መስከረም 01 ቀን 2011 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ቦልጋሪያ ( የድሮ በግ ተራ ) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕድሜያቸው የ19 እና የ20 ዓመት የሆኑ እህትማማቾችን የመኪና አደጋ በማድረስ የተሰወረው የፖሊስ መኪና አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል፤ ምርመራውን በማጣራት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ሲሆን ተከሳሹ አደጋውን ካደረሰ በኋላ ላለፉት 19 ቀናት ተሰውሮበት ከነበረው ከምስራቅ ጎጃም ደንባ ወረዳ በክትትል መያዙ ታውቋል፡፡ 
ተጠርጣሪውን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ አድካሚ ፍለጋ ማድረጉንም ተገልጧል፡፡ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚጻፉት ጉዳዮች ይልቅ፤ ወደ ኮሚሽኑ በመምጣት መረጃ ማግኘት የሚችል መሆኑ ተገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 1439ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዩች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡
አዲስ አበባ የአረፋበዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች አንዷ ነች፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የእምነቱ ተከታዩች በጋራ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሶላት ያደርጋሉ፡፡ በሶላት ወቅትም ይሁን ከዚያም በኋላ በዓሉ በሰላም እንዲያከበር ፖሊስ ኮሚሽኑ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡
በበዓሉ እለት በአዲስ አበባ ስታዲዩም እና በዙሪያው ፍተሻ መኖሩን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፍተሻ እንዲተባበር ፤ የእምነቱ ተከታዩች ለሶላት ሲመጡ የስለት መሳሪያዎችን እና ሌሎችአዋኪ ነገሮችን ይዞ ባለመምጣት የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ከፍተኛ አስተዋእፆ ማበርከቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ የዘንድሮ የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቀርቧል፡፡arefa


በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚደረገውን የሶላት ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-
• ከቦሌ ኦሎምፒያ  ፍላሚንጎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኡራኤል ባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ  ብሄራዊ ቤተ-መንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን
• ካሳንቺስብሄራዊ ቤተ-መንግስትፍልውሃ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ኦርማ ጋራዥ ፍልውሃ ሐራምቤ ሆቴል
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ኢሚግሬሽን ሐራምቤ ሆቴል ስታዲዬም
• ከጎማ ቁጠባ ብሄራዊ ቲያትር ስታዲዬም
• ከሰንጋ ተራ በድሉ ህንፃ  ስታዲዬም
• ከሰንጋ ተራ በለገሃር ስታዲዬም
• ከሜክሲካ አደባባይ በለገሃር ስታዲዬም
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድበለገሃር ስታዲዬም
• በሐራምቤ ሆቴል  ጋንዲ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጎተራ  በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ
ከቦሌ ወደ ኣራት ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
በኡራኤል በካሳንቺስ አራት ኪሎ
ከመገናኛ ወደ ጦር ኃይሎች መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
በኡራኤል  ካሳንቺስ ታላቁ ቤተ-መንግስት  እሪበከንቱ ቴዎድሮስ አደባባይ ኤክስትሪም ሆቴል  ተክለ ሀይማኖት  ጣር ሀይሎች
ከሳሪስ አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ እና ፒያሳ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ጎተራ  ወሎ ሰፈር  አትላስ ሆቴል  ኡራኤል  ካሳንቺስ  አራት ኪሎ ያሉ መንገዶችን በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡
ከዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ማታ ጀምሮ የሶላቱ ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ድረስ በስታዲዬም ዙሪያ እና አካባቢው በግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ ለጸጥታ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ከፈለገ በስልክ ቁጥሮች-
• 011-5-52-63-03
• 011-5-52-40-77
• 0115-52-63-02
• 011-1-11-01-11
ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዩች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡

Page 2 of 3

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus