×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 518

ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሃገር ቤት የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች አዲስ አበባ ፍፁም ሰላም የሰፈነባት ከተማ መሆኗን ማረጋገጣቸውን ተናገሩ፡፡በመላው ሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
*******
ኢትዮጵያ ተጣርታ አልቀርም በማለት ኑሯቸውን በተለያዩ ሃገራት ያደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሃገር ቤት በመግባት ላይ ናቸው፡፡
የዲያስፖራው ማህበረሰብ በቃ ወይም # NO MORE በሚል ጠንካራና ተከታታይ ሰልፍ በማድረግ የኢትዮጵያ ልሳን በመሆን የሀገራቸውን ድምፅ ሲያሰሙ መቆየታቸው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ሊቀመንበር አቶ እንድሪስ መሃመድ በተለይ ለአዲስ ፖሊስ ገልፀዋል፡፡ ማህበራቸው ልዩ ልዩ ሃገራዊ ጉዳዮችን በማስተባበር በውጪ የሚገኙ ዜጎች ለሃገራቸው እድገት እና ልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በአውሮፓ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አስተባባሪ አቶ ሰለሞን አሻግሬ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ሃገራችንን ያጋጠማትን ችግር ለመቅረፍ መላው ህዝብ እየተረባረበ እንደሆነና የዲያስፖራው ማህበረሰብም የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን በማስታወስ አሁን የተጀመረው የሃገርን ጥቅም የማስጠበቅ እንቅስቃሴን አጠናክረን በመቀጠል የሃገራችንን ችግር በዘላቂነት ልንፈታ ይገባል ብለዋል፡፡
ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ሚኒሶታ የሆነው ወ/ሮ ዘኒ ተሾመ ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት እንደመጡና እየተደረገ ባለው አቀባበል በጣም መደሰታቸውን አስረድተው ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ የገና በዓልን ለማክበር ወደ ላሊበላ ለመሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የመምጣታቸው ዋነኛ ምክንያት ስለ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት የሚነገረውን የተዛባ መረጃ ሃሰት መሆኑን ለመላው ዓለም ለማሳወቅና ለሃገራቸው እና ለወገናቸው ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት እንደሆነ ከአዲስ ፖሊስ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ሃሳባቸውን አጋርተውን ይህን በማድረጋቸውም ሀገራዊ ኩራት እንደተሰማቸው እንግዶቹ ገልፀዋል፡፡
የዲያስፖራ አባላቱ በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበው ከተማችን አዲስ አበባ ፍፁም ሰላም የሰፈነባት እንደሆነች በተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋውረው ማረጋገጣቸው አስታውቀው በመላው ሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡1111

መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ በአዲስ መንግስት ፣በአዲስ ተስፋ አዲስ ምዕራፍ የምትጀምርበት ቀን ነው ፡፡
የጋራ ግብረሀይሉ ከፌዴራል ፖሊስ፤ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት፤ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር አስቀድሞ ዕቅድ በማውጣት እና ህብረተሰቡን በማሰተባበር የተከናወኑት ተግባራት ውጤት አስገኝተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት የተከናወነው የአዲስ ምዕራፍ በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታ የጋራ ግብረሀይሉ አስታውቋል፡፡
ሥነ-ሥርዓቱ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅም በፍፁም ሙያዊ ብቃት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላትና ለሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች የፀጥታ የጋራ ግብረ-ሀይል ከፍ ያለ ምስጋናውን በታላቅ አክብሮት ያቀርባል፡፡
ለዜጎች ሰላም መረጋገጥ እንዲሁም የቁልፍ መሰረት ልማቶችን ደህንነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመጠበቅና ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ ለቀረፃ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሳሰበ፡፡
የሀገሪቱን ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው መሆኑን የጠቀሰው ተቋሙ አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ለቀረፃ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል፡፡
እነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡
ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀም እና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስጠንቅቋል።
መረጃውን ያገኘነው ከኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ ነው
ምናልባት የ'መረጃና ደህንነት የብሔራዊ ETHIOPIA እልግባል አገልግሎት NISS NATIONAL AND SECURITY INTELLIGENCE SERVICE' የሚል ጽሑፍ ምስል
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ አካባቢ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ም/ኢ/ር ጃፋር አሊ እና ኮንስታብል መስፍን በተለ የተባሉ የቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት አንዲትን ግለሰብ በአስነዋሪ ሁኔታ በመደብደባቸው በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጠራ ይገኛል፡፡
ህዝብን በሰብአዊነት ማገልገል የአዲስ አበባ ፖሊስ መርህ መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን አንዳንድ አመራሮችና አባላት ይህን መርህ በመተላለፍ የሚፈፅሙት ህገ-ወጥ ድርጊት ተቋሙ የማይታገስ መሆኑን ገልፆ በ2013 የበጀት ዓመት ብቻ እንኳን በልዩ ልዩ ጥፋት ላይ የተገኙ 171 የፖሊስ አመራሮችና አባላት ከሰራዊቱ እንዲሰናበቱ አድርጓል፡፡
ከስራ ከተሰናበቱት 29ኙ ከሰብአዊ መብት ጥስት ጋር በተያያዘ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል። ህግን በመተላለፍ ጥፋት በሚፈፁም አባላት እና አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፖሊስ አስታውቆ ህብረተሰቡ እንዲህ ዓይነት ከፓሊስ የሙያ ስነ- ምግባር ውጪ የሆኑ ድርጊቶች በሚፈፀሙበት ወቅት በፍጥነት ጥቆማ እንዲያደርግ እየገለፅን ግለሰቧን በደበደቡ የፖሊስ አባላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዶ ውጤቱን ለህዝብ የሚሳውቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ ስለሚመጡ እንግዶች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ መልዕክት ተላፏል፡፡
በሀገራችን የተካሄደውን 6ኛውን ብሔራዊ ምርጫ ተከትሎ የተወሰኑ ክልሎች መንግስት መመስረታቸው ይታወቃል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ፣ ጠቅላይ ሚኒስተሮች ፣ የሀገራት ተወካዮች እንዲሁም የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በሚገኙበት መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም የኢፌዲሪ መንግስት ይመሰረታል፡፡
የመንግስት ምስረታው በስኬት እንዲጠናቅ እንዲሁም የኢሬቻ እና የመስቀል በአላት በሰላም እንዲከበሩ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡
ግብረ ኃይሉ እቅድ በማውጣት እና ህዝብን በማሳተፍ ባከናወናቸው ተግባራት በዓላቱ በሰላም ተከብረዋል፡፡
ህብረተሰቡ በቅረቡ የተከበሩት የኢሬቻ እና የመስቀል በዓላት በሰላም እንዲከበሩ እንዲሁም በአጠቃላይ ለፀጥታው ስራ ስኬታማት እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ የሚበረታታ ነው፡፡
በአላቱ በሰላም እንዲከበሩ ህዝቡ እንደሁል ጊዜው ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ላደረገው ቀና ትብብር እንዲሁም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ኃላፊናታቸው በብቃት ለተውጡ የፀጥታ አካላት አመራሮችና አባላት የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን እያቀረበ የመንግስት መስረታው ፕሮግራሙ በውጤት እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ያስተላፋል፡፡
የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን እያቀረበ የመንግስት ምስረታው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-
1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር
2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ
3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ
4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል
5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን
6. ከአትላስ ሆቴል በደሳለኝ ሆቴል ሩዋንዳ
7. ከኤምፔሪያል ሆቴል ወደ ብራስ ሆስፒታል
8. ከገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል ውስጥ ውስጡን ወደ ብራስ ሆስፒታል
9. ከጎሮ አዲሱ መንገድ መሄጃ ወደ ብራስ ሆስፒታል
10. ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቀለበት መንገድ እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሩዋንዳ ማዞሪያ
11. ከካዲስኮ አደባባይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ዋናው ቀለበት መንገድ
12. ከቡልቡላ ወደ ቦሌ ሚካኤል
13. ከመስቀል ፍላውር ወደ ጎርጎሪዮስ አደባባይ
14. ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር አጎና ሲኒማ
15. ከጎፋ ማዛሪያ አዲሱ መንገድ መስቀለኛ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያ ለገሃር
16. ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ ገንት ሆቴል እንዲሁም ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
17. ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ኑር ህንፃ በባልቻ መስቀለኛ ወደ አረቄ ፋብሪካ
18. ከ18 ወደ ጦር ሃይሎች 3 ቁጥር ማዞሪያ የሚወስደው ከላይም ከታችም
19. ከሞላ ማሩ ወደ ቅድስት ልደታ ቤተ-ክርስቲያን
20. ከተክለ ሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ወደ ዲ-አፍሪክ ሆቴል
21. ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
22. ከአብነት ፈረሳኛ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
23. ወሎ ሰፈር፣ ኦሎምፒያ፣ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግስት ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ ሸራተን አዲስ አራት ኪሎ
24. ጎርጎሪዮስ አደባባይ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ለትራፊክ ዝግ ሲሆኑ ፕሮግራሙ በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ አካባቢ ከዛሬ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ/ ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫዎች ግራና ቀኝ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት ግብረኃይል አስታውቋል፡፡
እንግዶች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ መልዕክቱ አስተላልፏ ።
ፎቶው ዝርዝር መግለጫ የለዉም
 

slide new1

August 07, 2018 0 comment

37749376 2086514781597100 7220517852019687424 nAddis Ababa Police Commission

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው አመራሮችና አባላት በሦስት ዙር የሠጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀቀ፡፡ ወቅቱ የሚጠይቀውን ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው ገልፀዋል፡፡3
በኮሚሽኑ ከመጋቢት 9 እስከ ሚያዚያ 9 ቀን 2011 ዓ/ም በሦስት ዙር ለመላው አመራሮችና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ሚያዚያ 10 ቀን 2011 ዓ/ም በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የፀጥታ አካላትን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 2
ኮሚሽነር ጀነራሉ አያይዘው ሀገራችን በለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝድ እና ለውጡ ህዝባዊና ህገ-መንግስታዊ መሆኑን በመጥቀስ በህዝብ ፍላጎት የመጣው ለውጥ የታለመለትን ግብ እንዲመታ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡3
ለውጡ በፖሊስ ተቋማት ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የጠቁሙት ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከምንም በላይ ለሰው ሀብት ልማት እና ለኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የፖሊስ አመራሮችና አባላት የለውጡን ባህሪ ተገንዝበው በተለይ ሰብዊ መብቶችን አክብረው በማስከበር ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ህዝብና መንግስት ቅን አገልጋይ እንደሚፈልጉ ተናግረው ኮሚሽኑ የለውጡ አካል በመሆን ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የፖሊስ ተቋም በመገንባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገችና እየዘመነች ለምትገኘው ከተማችን የሚመጥን የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ 54
ስልጠናው የአመራሮችን እና የአባላትን የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት የራሱ ጠቀሜታ ማበርከቱን ኮሚሽነር ጌቱ በንግግራቸው ጠቁመው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በቅርበት ከሚሰሩ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎ ሺፕ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ ልዩ ልዩ መልክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን ተቋማቸው ለፀጥታ አካላት የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡በአስራ ሦስት የተለያዩ ስፍራዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተደግፎ በተሰጠው ስልጠና ላይ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ስልጠናውን ተከታትለውታል፡፡

Page 1 of 3

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus